News & Events

ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ ባሳለፍነው በጀት ዓመት ከ636 ሚሊዮን ብር በላይ ያልተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡን አስታወቀ

ቅርንጫፎቹን ወደ “የደንበኞች ቤት” መቀየሩን አስታወቀ

ባሳለፍነው በጀት ዓመት በመላው ሀገሪቱ ውስጥ በርካታ ማህበራዊ፤ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች የተከሰቱበት ዓመት ሆኖ ቢያልፍም  ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ109 ነጥብ 5 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ 636 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ጠቅላላ ትርፍ ማስመዝገብ መቻሉን አስታወቀ።

 

ህዳር 17 ቀን 2024 ዓ.ም በሸራተን አዲስ በተካሄደው 30ኛው የኒያላ ኢንሹራንስ የባለአክሲዮኖች 30ኛ ዓመታዊ አጠቃላይና 23ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር ዶ/ር ሳራ ሱሩር የኩባንያውን አመታዊ የስራ አፈጻጸም አስመልክቶ ለባለ አክሲዮኖች ባቀረቡት ሪፖርት ላይ እንደገለጹት 2016 ዓ.ም  በጀት ዓመት ለኩባንያው ውጤታማ ነበር፡፡

በ2022/23 በጀት ዓመት ከነበረው 303 ነጥብ 7 ሚሊዮን አጠቃላይ ትርፍ ወደ ብር 634 ነጥብ 4 ሚሊዮን በማሳደግ ካለፈው ዓመት አሃዝ በእጥፍ ብልጫ አሳይቷል ያሉት ሊቀመንበሯ በመሆኑም በበጀት ዓመቱ በአንድ አክሲዮን የተገኘው ገቢ ከብር 354 ወደ ብር 502 ከፍ በማለት የ42 በመቶ ጭማሪ በማስመዝገቡ ለኩባንያው ባለሀብቶች እንኳን ደስ ያላችሁ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

 

 

ዶ/ር ሣራ አያይዘው እንደገለጹት ኩባንያው ከጠቅላላ ኢንሹራንስ ሽፋን (General insurance ) ከ1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ዐረቦን በመሰብሰብ የ20 በመቶ ዕድገት ያስመዘገበ ሲሆን የህይወት እና ታካፉል ኢንሹራንስ አገልግሎቶች ደግሞ በቅደም ተከተል የ18 ነጥብ 7 በመቶና የ7 ነጥብ 6 በመቶ እድገት አሳይተዋል፡፡

An overview

Nyala Insurance Share Company (NISCO) was founded in July 1995 following the liberalization of the insurance business to the private sector in 1994 with the Licensing and Supervision of Insurance Business Proclamation No. 85/1994. Read more...

Investments

Apart from its major investments in real estates in the downtowns of Addis Ababa, Bahir Dar and Nazareth, Nyala Insurance selectively invests in various financial institutions like Dashen Bank, which have potentially high investment returns. Read more...

Links

Contact us

Protection House, Mickey Leland Street

Tel: +251-11-6626679/80/76

-->