News & Events

ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ ዐረቦን ማግኘቱን ገለጸ

 

የኩባንያውጠቅላላ የተከፈለ ካፒታል ከብር 830 ሚሊዮን ወደ 1 ነጥብ 08  ቢሊዮን  ከፍ እንዲል የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ወሰነ። 

 

ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. ባሳለፍነው በጀት ዓመት  በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ  ዐረቦን መሰብሰቡን፤  ይህም መጠን  ካምናውጋርሲነጻጸርየ47 በመቶእድገት ማስመዝገቡን ገለጸ::

ኩባንያው 29ኛውን መደበኛና 22ኛዉን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ኅዳር 1 ቀን 2016 ዓ.ም   በሸራተን  አዲስ ባካሄደበት ወቅት የኩባንያው ዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር ዶ/ር  ሣራ ሱሩር  ባቀረቡት ዓመታዊ ሪፖርት ላይ እንደተገለጸው ያሳለፍነው በጀት ዓመት በሀገሪቱ ውስጥ የቢዝነስ አውዱን የሚያውኩ በርካታ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ችግሮች የተከሰቱበት ዓመት ቢሆንም ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ.  ከቢሊዮንብርበላይበማለፍእጅግ  አመርቂውጤትለማስመዝገብየቻለበትዓመትነበር፡፡

ዶ/ር  ሣራ ሱሩር  አያይዘው እንደገለጹት  ከተገኘው ጠቅላላ ዐረቦን ውስጥ  1 ነጥብ1 ቢለዮንወይም80 በመቶየሚሆነውገቢየተገኘውከጠቅላላመድንሽፋን(general insurance) ነው፡፡

በሌላ በኩል በተጠናቀቀውበጀትዓመትኩባንያውየብር303 ነጥበ6 ሚሊዮንብር ያልተጣራ ትርፍለማመዝገብየቻለሲሆን  ከአምናውትርፍጋርሲነጻጸርበ15 ነጥብ4 በመቶወይምበ40 ነጥብ6 ሚሊዮንብር  የላቀሆኖተገኝቷል ያሉት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር  ለዚህታላቅውጤትመገኘትከፍተኛሚናለተጫወቱትየኩባንያውማኔጅመንትአባላትናመላውሠራተኞች ምስጋና አቅርበዋል።

የኩባንያው ጠቅላላ የሀብት መጠን ያለፈው ዓመት ከነበረበት 3 ቢሊዮን ወደ 3 ነጥብ 8 ቢሊዮን ማደጉን፤ ይህም ካምናው ጋር ሲነጻጸር የ28 ነጥብ 7 በመቶ ብልጫ እንዳለው የቦርዱ ሊቀ መንበር ካቀረቡት ዓመታዊ ሪፖርት መረዳት ይቻላል፡፡

የተገኘውአመርቂውጤትኩባንያውበወሰደውጥንቃቄየተሞላበትየሥጋትአመራርሥርዓት(Prudent Risk Management) ፤ እንዲሁምየደንበኞችንፍላጎትያማከሉአዳዲስየዋስትናዓይነቶችንለመስጠትናአዳዲስደንበኞችንለማፍራትበመቻሉ እንደሆነም  ዶ/ር ሣራ  ተናግረዋል።

እንደ ዶ/ር ሣራ ገለጻ በከፍተኛመጠንበመናርላይያለውንየካሳክፍያወጪለመቆጣጠርኩባንያውየተለያዩአሰራሮችንማስተዋወቅናመተግበርየተጀመረቢሆንምበበጀትዓመቱየነበረውየካሳክፍያመጠንካለፈውዓመትጋርሲነጻጸርበ77 ነጥብ1 በመቶከፍ ብሎ ታይቷል፡፡ በመሆኑም ኩባንያውበበጀትዓመቱ ለደንበኞቹ በጠቅላላውከ370 ሚሊዮንብርበላይየሆነ ካሣከፍሏል።

በሌላ በኩል ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. ሙሉ በመሉ የዲጂታል ኢንሹራንስ አገልግሎት አሰጣጥን ታሳቢ ያደርገ የአምስት ዓመት ስትራተጂክ ዕቅድ ቀርጾ ወደ ሥራ መግባቱን የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ያሬድ ሞላ  ገልጸዋል። እጅግ በርካታ የሆነውን የህብረተሰብ ክፍል በተለይም“ዲጂታል ኔቲቭ” እየተባለ የሚጠራው ወጣቱ የኅብረተሰባችን ክፍል የኢንሹራንስ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድርግ፤ አዳዲስ አገልግሎቶችን ለማቅረብ፤ ለደንበኛው ቀላልና ምቹ የሆኑ አሰራሮችን ለመዘርጋት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ ይገኛልም ብለዋል።

እንደ አለፉት ተከታታይ ዓመታት ሁሉ ዘንድሮም ከተገኘው የተጣራ ትርፍ ላይ ብር 254 ነጥብ 5ሚሊዮን ካፒታል ለማሳደግ እንዲውል  ጉባኤ በሙሉ ድምጽ የተወሰነ ሲሆን ይህም የኩባንያውን ጠቅላላ የተከፈለ ካፒታል መጠን ከብር 1.08 ቢሊዮን በላይ ያደርሰዋል፡፡

ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. በ1987 ዓ.ም በብር ሰባት ሚሊዮን የተከፈለ ካፒታል የተቋቋመ አንጋፋ የኢንሹራንስ ተቋም ሲሆን በአሁኑ ጊዜ  በ48 የአገልግሎት ማዕከላት በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች የተሟላ አገልግሎት መስጠት ላይ ይገኛ። 

An overview

Nyala Insurance Share Company (NISCO) was founded in July 1995 following the liberalization of the insurance business to the private sector in 1994 with the Licensing and Supervision of Insurance Business Proclamation No. 85/1994. Read more...

Investments

Apart from its major investments in real estates in the downtowns of Addis Ababa, Bahir Dar and Nazareth, Nyala Insurance selectively invests in various financial institutions like Dashen Bank, which have potentially high investment returns. Read more...

Links

Contact us

Protection House, Mickey Leland Street

Tel: +251-11-6626679/80/76

-->