News & Events

አቶ ያሬድ ሞላ የአፍሪካ ኢንሹራንስ ድርጅት (AIO) ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ

 

በናሚቢያ ዋና ከተማ ዊንድሆክ በተካሄደው 50ኛው የአፍሪካ ኢንሹራንስ ድርጅት(African Insurance Organisation-AIO) ዓመታዊ ጉባዔ ላይ የኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ያሬድ ሞላን የድርጅቱ ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ ሾመ::

መቀመጫውን በካሜሩን ዋና ከተማ ያውንዴ ያደረገው የአፍሪካ ኢንሹራንስ ድርጅት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1972 ዓ.ም የተመሠረተ መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም ሲሆን ዋና ግቡም በመላው አፍሪካ የኢንሹራንስ ኢንደስትሪው በውድድር ላይ የተመሠረተ ጤናማ ዕድገት እንዲያስመዘግብ አስተዋጽኦ ማድረግ ነው ::

ድርጅቱ ሰሞኑን  50ኛውን ጠቅላላ ዓመታዊ ጉባዔ በናሚቢያ ርዕሰ መዲና ዊንድሆክ አካሂዶ ሲያጠናቅ የኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ.ዋናሥራአስፈጻሚ  አቶ ያሬድ ሞላን የድርጅቱ ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ  ሾሟል ::

በድርጅቱ አሠራር መሠረትም በሚቀጥለው ዓመት አቶ ያሬድ ከምክትል ፕሬዚዳንትነት ወደ ዋና ፕሬዚዳንትነት እንደሚያድጉ ይጠበቃል ::

አቶ ያሬድ  በ2019 ዓ. ም(እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር)  በመላው አፍሪካ ከሚገኙ የኢንሹራንስ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር ተወዳድረው ባሳዩት ብቃት ያለው አመራር የዓመቱ ምርጥ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተብለው መሸለማቸው ይታወሳል ::

በሌላ በኩል እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር  በ2025 ዓ.ም  የሚካሄደውን የድርጅቱን 51ኛ ጠቅላላ ዓመታዊ ጉባዔን  ኢትዮጵያ እንድታዘጋጅ ተመርጣለች ::

አቶያሬድ  በአሁኑጊዜ  የኢትዮጵያ መድን ሰጪዎች ማኅበርን (Association of Ethiopian Insurers-AEI)) በፕሬዚዳንትነት በመምራት ላይ የሚገኙ ሲሆን  በፈረንሳይ Paris School of Business  የፒኤችዲ  ትምህርታቸውን በመከታል ላይ ናቸው:: በኢንሹራንስ ኢንደስትሪው ላይም ከ30 ዓመታት በላይ የካበተ ልምድ አላቸው::

 

An overview

Nyala Insurance Share Company (NISCO) was founded in July 1995 following the liberalization of the insurance business to the private sector in 1994 with the Licensing and Supervision of Insurance Business Proclamation No. 85/1994. Read more...

Investments

Apart from its major investments in real estates in the downtowns of Addis Ababa, Bahir Dar and Nazareth, Nyala Insurance selectively invests in various financial institutions like Dashen Bank, which have potentially high investment returns. Read more...

Links

Contact us

Protection House, Mickey Leland Street

Tel: +251-11-6626679/80/76

-->